Ethiopic Font Test

Droid Sans, Droid Ethiopic

በህጻንነቱ

ሱሰኒዩስ የተወለደው የአህመድ ግራኝ ሰራዊት ከተሸነፈ በኋላ ሲሆን በዚህ ጊዜ የህዝብ ንቅናቄ ይታይ ነበር። የሱሰኒዮስ ዜና መዋዕል እንደሚያትተው በህፃንነቱ ከአባቱ ጋር ጎጃም ውስጥ ይኖሩበት የነበረው ከተማ በአንድ ተንቀሳቃሽ የኦሮሞ ቡድን ስር ወደቀ ፤ አባቱና ቀሪው የከተማው ሰው ሲገደል እሱ ግን ለአንድ አመት ከግማሽ በምርኮ ከኦሮሞው ቡድን መሪ ጋር ተቀመጠ። ከዚያ በኋላ የኦሮሞው ቡድን በዳሞት ከደጅ አዝማች አስቦ ጋር ጦርነት ለመግጠም ሞክሮ በመሸነፉ ወደአካባቢው ዋሻወች በመግባት ለመሸሸግ ሞከረ። የደጃአዝማች አስቦ ሰራዊት የተሸሸጉትን ቡድኖች አባላት እዋሻው ድረስ በመግባት ከነመሪያቸው በሰንሰለት አሰሩዋቸውና "ህጻኑን ሱሰኒዮስ ካመጣችሁ ትለቀቃላችሁ ካላመጣችሁ ግን ትገደላላችሁ" አላቸው። ሱሰኒዮስ በዚህ መንገድ ሲለቀቅ፣ ደጃች አስቦ ህጻኑን መንገዱ ለተባለ የአቤቶ ፋሲለደስ ወዳጅ በአደራ ሰጡት። መንገዱም የንግስት አድማስ ሞገሴ (የአፄ ሰርፀ ድንግል እናት) ቤተኛ ስለነበር ህጻኑ ከንግስቲቱ ዘንድ አደገ ። [2] [ለማስተካከል]ወህኒና አጼ ያዕቆብ